ፍኖተ ጽድቅ ዘተዋሕዶ Finote Tsidk 2.0

«ፍኖተ ጽድቅ ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ» በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓት፣ ቀኖና እና ትውፊት መሠረት ዶግማ ቤተ ክርስቲያንን ጠብቆ ከ፲፪ መጻሕፍት በላይ ተካተውበት የቀረበ የመጻሕፍት መድብል ነው።
ይህ የመጻሕፍት መድብል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የትርጓሜ ሊቃውንት የተራቀቁባቸውን እና የተጠበቡባቸውን ሲወርዱ ሲወራረዱ ለእኛ የደረሱ የትርጓሜ መጻሕፍት የተካተቱበት ነው። በሦስት ዐበይት ክፍሎች የተመደቡ መጻሕፍተ ቤተ ክርስቲያንን ያካተተው ይህ መድብል ምክርና ተግሳጽንም የያዘ ስለሆነ ብዙዎች እንደሚወዱት ተስፋ እናደርጋለን። በአዘጋጁ ታትመው የቀረቡና እና ለኅትመት ዝግጁ የሆኑ መጻሕፍትም የተካተቱበት ስለሆነ ልዩ ያደርገዋል። በአዘጋጁ ከቀረቡ መጻሕፍት መካከል በቅብዐት ምንፍቅና አማኞች ለተጻፉ መጻሕፍት ተገቢ ምላሽ የተሰጠባቸውን «ደብረ አሚን - የሃይማኖት ተራራ» እና «ፍኖተ ጽድቅ - የእውነት ጎዳና» አካተናል። ከዚህ በተጨማሪም አዘጋጁ የጻፋቸው የተለያዩ ወጎች፣ ትምህርቶችና ግጥሞችም ምክርና ተግሳጽን በስፋት አካተው ቀርበውበታል። ከእግዚአብሔር ለምን እንርቃለን? እግዚአብሔርስ ከእኛ ለምን ይርቃል? የሚለውን መሠረታዊ ጥያቄ የሚመልስ እና ወደ ንስሐ የሚመራ «ለምን ርቀህ ቆምህ?» የተሰኘው የአዘጋጁ መጽሐፍም በዚሁ መድብል ውስጥ የተካተተ ነው። እነዚህ የአዘጋጁ መጻሕፍት ገበያ ላይ የማይገኙ መሆናቸው ይህን መተግበሪያ ልዩ ያደርገዋል።
ይህ መተግበሪያ በተጨማሪነት ቤተ ክርስቲያናችን ከዓመት እስከ ዓመት የምትገለገልባቸውን ድንቅ መጻሕፍት ሃይማኖተ አበውንና መጽሐፈ ስንክሳርን ያካተተ ነው።
ይህ መተግበሪያ የያዛቸው መጻሕፍት ዝርዝር

፩. የአንድምታ ትርጓሜ ክፍል
- የጸሎተ ሃይማኖት አንድምታ ትርጓሜ።
-የውዳሴ ማርያም አንድምታ ትርጓሜ።
- የቅዳሴ ማርያም አንድምታ ትርጓሜ።
- የአራቱ ወንጌል አንድምታ ትርጓሜ።

፪. የአዘጋጁ መጻሕፍት ክፍል
- ደብረ አሚን
- ፍኖተ ጽድቅ
- ለምን ርቀህ ቆምህ?
- አማኞችን ማጽናትና ማበርታት
- ወጎች
- ትምህርቶች
- ግጥሞች

፫. ሌሎች መጻሕፍት ክፍል።
- ሃይማኖተ አበው
- መጽሐፈ ስንክሳር
- ፍኖተ እግዚአብሔር

Celkové hodnocení

Průměr hodnocení
3

Pro hodnocení programu se prosím nejprve přihlaste

Přejít do Google Play

Souhrnné informace o ፍኖተ ጽድቅ ዘተዋሕዶ Finote Tsidk

  • Verze programu

    2.0
  • Autor

  • Potřeba instalace

    ne
  • Velikost souboru

    8,6 MB
  • Staženo

    26× celkem
    0× tento měsíc
  • Poslední aktualizace

    22. 10. 2019

Něco jsme propásli?

Dejte nám vědět. Upozornit redakci Stahuj
Velice děkujeme za Vaše podněty